Coronavirus (COVID-19) update: Temporary changes to Victoria’s laws on renting homes. Find out more
ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።
በResidential Tenancies Act 1997 አንቀጽ ህግ መሰረት ያለዎን ግዴታ አንዱን ወይም ከዚያ በላይ አላሟሉም ብሎ ባለንብረቱ ካመነበት ለግዴታ መጣስ ማስጠንቀቂያ ይሰጥዎታል።
የተከራዮች ግዴታዎች ምንድ ናቸው?
በግዴታ መጣስ ማስጠንቀቂያ ላይ ምን መካተት አለበት?
ማካካሻ ገንዘብ እና ህጋዊ የሆነ ትእዛዝ
ለማስለቀቅ ማስጠንቀቂያ
ለባለንብረቱ የግዴታ መጣስ ማስጠንቀቂያ ስለመስጠት
በአንቀጽ ህጉ መሰረት በሚከተለው ዝርዝር የተከራይ ግዴታዎችን ያሳያል። በነዚህ ግዴታዎች መሰረት ተከራዩ ማድረግ ያለበት:
የግዲታ መጣስ ማሳሰቢያ መደበኛ ማስጠንቀቂያ ሲሆን እንደ ተከራይ መጠን ‘የግዴታ መጣስ ተግባርዎን’ ማቆም እንዳለብዎ እና/ወይም ማስጠንቀቂያው እንደደረስዎ በ14 ቀናት ውስጥ የገንዘብ ማካካሻ መክፈል አለብዎት። ይህንን ካላደረጉ፤ የማስፈጸሚያ ህጋዊ ትእዛዝ በVictorian Civil and Administrative Tribunal እንዲሰጥ ባለንብረቱ ማመልከት ይችላል።
የግዴታ መጣስ ማስጠንቀቂያ ህጋዊነት ማግኘት እንዲችል:
በግዴታ መጣስ እና በተከራይና አከራይ ስምምነት (ኮንትራት) ውል መጣስ መካከል ልዩነት አለ። ለምሳሌ፡ የቤት እንስሳት ማስቀመጥ የርስዎን ተከራይና አከራይ ስምምነት ውል መጣስ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን በአንቀጽ ህግResidential Tenancies Act 1997 መሰረት ለግዲታ ውለታን መጣስ አይደለም። ለተከራይና አከራይ ስምምነት ውል ጊዜ ገደብ መጣስ ባለንብረቱ ለግዲታ ውለታ መጣስ የሚል ማስጠንቀቂያ ሊሰጥ አይችልም፤ ነገር ግን ህጋዊ ትእዛዝ እንዲሰጥ ለልዩ ፍርድ ቤቱ ማመልከት ይችላሉ።
ባለንብረቱ የማካካሻ ገንዘብ እና/ወይም ህጋዊ ትእዛዝ ለማግኘት ለVictorian Civil and Administrative Tribunal ካመለከቱ ታዲያ ላመለከቱበት ቅጽ ቅጂውን ለርስዎ መላክ አለባቸው። ከዚያም የፍርድ ችሎቱ የሚካሄድበትን ሰዓት፣ ቀንና ቦታ በልዩ ፍርድ ቤቱ በኩል ማሳሰቢያ ይደርስዎታል። ባለንብረቱ ባቀረበው ጥያቄ ላይ ለመከራከር ከፈለጉ በልዩ ፍርድ ቤቱ ችሎት ስያሜ ላይ መቅረብ አለብዎት። በፍርድ ችሎቱ ላይ ካልሄዱ እርስዎ በሌሉበት ጉዳዩ ይታይና ባለንብረቱ በርስዎ ላይ ላቀረበው ጥያቄ ለማሸነፍ ጥሩ እድል ይከፍትለታል።
ባለንብረቱ ባቀረበው ጥያቄ እና/ወይም የማካካሻ ገንዘብ መጠን ስለመቀነስ በልዩ ፍርድ ቤቱ ችሎት ላይ ለመከራከር እድሉ ይሰጥዎታል።
በአንቀጽ ህጉ Residential Tenancies Act 1997 መሰረት እርስዎ ህጉን እንደጣሱ ባለንብረቱ ልዩ ፍርድ ቤቱ ማሳመን ስላለበት ታዲያ ላቀረቡት ጥያቄ የሚደግፍ ማስረጃ ስለሚያቀርቡ፤ እርስዎን ይህንን ለመከላከል ዝግጅት ማድረግ አለብዎት (ለምሳሌ፡ ፎቶግራፎች፣ ምስክር በአካል ወይም የምስክር ህጋዊ ጽሁፍ ማስረጃ ማምጣት)።
የግዴታ መጣስ ማስጠንቀቂያ ከተሰጥዎት በኋላ በ14 ቀናት ውስጥ ግዴታዎን አልተወጡም ብሎ ባለንብረቱ ካመነበት ሁለተኛ ማስጠንቀቂያ ሊሰጥዎት እንደሚችል እና/ወይም ህጋዊ የሆነ ትእዛዝ ለማግኘት ወደVictorian Civil and Administrative Tribunal ማመልከት ይችላሉ። ልዩ ፍርድ ቤቱ ለባለንብረቱ የሚደግፍ ትእዛዝ ከሰጠ እና ካልተቀበሉት ባለንብረቱ የ14 ቀን ከቤት ማስለቀቂያ ማስጠንቀቂያ ሊሰጥዎት ይችላል።
በልዩ ፍርድ ቤቱ የተሰጠን ትእዛዝ ባለመቀበል የ Consumer Affairs Victoria ክስ መመስረት ሲችል ይህም ሁለቱንም ማለት በገንዘብም ሆነ ገንዘብ ነክ ባልሆነ ትእዛዝ ላይ ተግባራዊ ይሆናል። በሚታተምበት ጊዜ ቅጣቱ $2442.80 ዶላር በተጨማሪም ትእዛዙ ተቀባይነት እስኪያገኝ ድረስ በየቀኑ $610.70 ዶላር፤ ከፍተኛ መጠን እስከ $7328.40 ዶላር ይሆናል።
እንዲሁም ተመሳሳይ ግዴታን ለሶስተኛ ጊዜ ከጣሱ እና ቀደም ሲል በነበሩት ሁለት የህጋዊ ግዴታን መጣስ ማስጠንቀቂያ ተሰጥትዎት ከነበረ ባለንብረቱ ወደ ልዩ ፍርድ ቤቱ ሳይሄድ የ14 ቀን ማስለቀቂያ ማስጠንቀቂያ ሊሰጥዎት ይችላል።
በአንቀጽ ህግ Residential Tenancies Act 1997 መሰረት ባለንብረቱ ያለበትን ግዴታ አልተወጣም ብለው ካሰቡ እንደ ተከራይ መሆንዎ መጠን የግዴታ መጣስ ማስጠንቀቂያ ለባለንብረቱ መስጠት ይችላሉ።
ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።
ስለ ባለንብረቶች ወይም ንብረት ተወካዮች ቅሬታዎች
ለማካካሻ ክፍያ ጥያቄ ስለመከራከር
የግዲታ መጣስ ማሳሰቢያ ለባለንብረትዎ ስለመስጠት
በቪክቶሪያ ሲቪልና አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት
ተጨማሪ መረጃ ወይም እርዳታ ካስፈለግዎት እባክዎ እኛን ያነጋግሩ።
When you get a breach of duty notice | Amharic | September 2011