Coronavirus (COVID-19) update: Temporary changes to Victoria’s laws on renting homes. Find out more
ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።
በጊዜ የተወሰነ የቤት ኪራይ ስምምነት (ውል) ቢኖርዎትም እንኳን በኪራዩ ወቅትም ቢሆን አከራዩ ቤቱን ለመሸጥ ይችላል፡፡ ኪራይዎ እንደ ተለመደው ይቀጥላል ፡፡
የቤቱ ባለቤት ቤቱን እየሸጠ ነው ማለት እርስዎ ቤቱን ለቅቀው መውጣት ይኖርብዎታል ማለት አይደለም፡፡ አከራዩ ቤቱን ለቅቀው እንዲወጡ ከፈለገ የመልቀቂያ ማስታወቂያሊሰጥዎት ይገባል፡፡
በቤቱ ሽያጭ ምክንያት አከራዩ ቤቱን እንዲለቁለት ከፈለገየመልቀቂያ ማስታወቂያ ይሰጥዎታል፣የመልቀቂያ ማስታወቂያው ጊዜ እንዳበቃ አከራዩ ወዲያውኑ ቤቱ ባዶ እንደሆነ ለመሸጥ ከፈለገ፡፡ አከራዩ የቤት ሽያጭ ውል ፈጽሞ ከሆነና እርስዎ ቤቱን ለቅቀው እንዲወጡ የሚፈልግ ከሆነ የሽያጭ ውሉን በፈጸመ በ14 ቀናት ውስጥ ወይም ሁሉም የውሉ ሁኔታዎች ከተሟሉየመልቀቂያ ማስታወቂያ ሊሰጥዎት ያስፈልጋል፡፡ ይህ ማለት የቤቱን የሽያጭ ውል ከፈረመ ከጥቂት ወራት በኋላ ሲያስብበት ቆይቶ በመልቀቂያ ማስታወቂያው ላይ ሽያጩን እንደምክንያት ሊጠቅስ አይችልም ማለት ነው፡፡
የመልቀቂያ ማስታወቂያውን እርስዎ ቤቱን እንዲለቁላቸው ከሚፈልጉበት ቀን ቢያንስ ከ60 ቀናት በፊት መስጠት ይገባቸዋል፡፡
በጊዜ የተወሰነ የኪራይ ውል ካለዎት ይህ የተወሰነ ጊዜ እስከሚያለቅ ድረስ በቤቱ ውስጥ ለመቆየት መብት አለዎት፡፡ ስለዚህ እርስዎ ቀደም ብለው ካልተስማሙ በስተቀርበመልቀቂያ ማስታወቂያውላይ የሚጠቀሰው ቀን በውልዎ ላይ ከተጠቀሰው የተወሰነ ጊዜ በፊት ሊሆን አይችልም፡፡
በጊዜ የተወሰነ የኪራይ ውል ካለዎትና ቤቱ እየተሸጠ (ወይም የተሸጠ) በመሆኑ ምክንያት እርስዎ ከቤቱ ቀደም አድርገው መልቀቅ ከፈለጉ አከራዩ የሚስማማ ከሆነ የኪራይ ውሉን አስቀድመው ማቋረጥ ይችላሉ፡፡
ስምምነቱን በጽሁፍ አድርገው አከራዩ ወይም ወኪሉ እንዲፈርሙበት ካላደረጉ በስተቀርየውል ማፍረሻ ክፍያ እንዲከፍሉ ሊደረጉ ይችላሉ፡፡
ወቅታዊ የሆነ የኪራይ ውል ካለዎት (ለምሳሌ ከወር እስከ ወር) እና60 ቀን የመልቀቂያ ማስታወቂያከደረሰዎት ይህ የ60 ቀን ጊዜ ከማብቃቱ በፊት ቤቱን ለቅቀው መውጣት ይችላሉ ነገር ግን ከመልቀቅዎ በፈት ለአከራይዎ ወይም ለአዲሱ ባለቤት ቤቱን ከመልቀቅዎ ቢያንስከ14 ቀናትበፊት የጽሁፍ ማስታወቂያ መስጠት ይኖርብዎታል፡፡ ከዚህ ቀን አስቀድመው ቤቱን የሚለቁም እንኳን ቢሆን ለእነዚህ 14 ቀናት የቤት ኪራይ መክፈል አለብዎት፡፡
በጊዜ የተወሰነው የኪራይ ዘመን ከማብቃቱ በፊት አከራዩ ቤቱን እንዲለቁለት ቢፈልግ ለሚደርስብዎት ጉዳትካሣ እንዲከፈለዎት ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡ ካሣውን ለመክፈል ከተስማሙ ስምምነቱን በጽሁፍ ያስፍሩትና በእርስዎ እና የንብረቱ ባለቤት በሆነውና ካሣውን ለመክፈል በተስማማው ሰው ወኪሉ በሆነው በአሁኑ ባለቤት ወይም በአዲሱ ባለቤት መፈረሙን ያረጋግጡ፡፡
እንደተከራይ በተከራዩት ቤት ውስጥ‘በጸጥታና በሰላም የመኖር’ መብትያለዎት በመሆኑ አከራዩ ወደ ቤትዎ ለመምጣት ቢፈልግ ይህንን መብትዎን በማክበር መሆን ይኖርበታል፡፡
ቤቱን ገዥ ለሚሆኑ ሰዎች የበለጠ ማራኪ እንዲመስል ለማድረግ የተለየ ጥረት ወይም ወጪ (ለምሣሌ እርስዎ የማይገባ የጽዳት ድካም ውስጥ መግባት ወይም የጽዳት ሥራ የሚሰሩ ሰዎችን መቅጠር) እንዲያደርጉ አይጠበቅብዎትም፡፡ እርስዎ በሕግ መሠረት የሚጠበቅብዎት በማናቸውም ሁኔታ በመደበኛነት የሚጠበቅ ሥፍራውን ንጹህ አድርጎ የመያዝ ሥራ ነው፡፡
ወደ ቤትዎ ለመግባት በሕግ የሚፈለጉትን ሁሉንም መሥፈርቶች ካሟላ አከራይዎ ‘ቤቱን ለመግዛት ለሚፈልግ ሰው’ ለማሳየት መብት አለው፡፡
ምንም እንኳን አከራዩ ‘ቤቱን ለመግዛት በሚፈልግ ሰው’ አማካይነት ለማሳየት የሚችል ቢሆንም አሁን በሥራ ላይ ባለው ሕግ መሠረት ‘ለምርመራ ክፍት ያድርጉ’ የማለት መብትየሌለውሲሆን እርስዎም ለዚህ የአከራዩ ጥያቄ ቤትዎን እንዲከፍቱ አይጠበቅብዎትም፡፡ Higgerson v Ricco (Residential Tenancies) [2014] VCAT 1214.)
አከራዩ (ወይም ወኪሉ) ቤቱን ለመግዛት ከሚፈልግ ሰው ጋር ወደ ቤትዎ መግባት የሚችሉት፡
ቤቱን ለመግዛት የሚፈልገው ሰው ቤቱን ለማይት ከሚያስፈልገው ሰዓት በላይ መቆየት አይችሉም፡፡
አከራዩ በሕግ የሚጠየቁ ሁሉንም መሥፈርቶች ካሟላ እና ተገቢውን ማስታወቂያ ከሰጠዎት እርስዎ ቤት ውስጥ ቢኖሩም ባይኖሩም ለመግባት ይችላል፡፡
ምንም ዓይነት ማስታወቂያ ያልደረሰዎ ከሆነና አከራዩ ወይም ወኪሉ ሲመጡ እርስዎ ቤት ውስጥ ከሆኑ እንዲገቡ መፍቀድ አይኖርብዎትም፡፡
እንደ ድንገተኛ አደጋ የመሰለ በቂ ምንያት ከሌላቸው በስተቀር የእርስዎን ስምምነት ካላገኙና ተገቢውን ማስታወቂያ ያላደረሱዎት ከሆነ አከራዩ ወይም ወኪሉ ቤትዎ ውስጥ ከገቡ እንደ ወንጀል ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ይህን የሕግ ጥሰት ለConsumer Affairs Victoriaማመልከት የሚችሉ ሲሆን አከራዩ ወይም ወኪሉ ሕጉን ያልተከተሉ ከሆነ ሕግ የመጣስ ማስታወቂያ ሊያወጣባቸው ይችላል፡፡
ንብረቱን በመሸጥ ሂደት ውስጥ ወኪሎች አብዛኛውን ጊዜ በሽያጭ ሰሌዳ ላይ ለማድረግ እና ለኢንተርኔት ማስታወቂያም የቤቱን ፎቶግራፍ ይፈልጋሉ፡፡
ንብረቱን ለመሸጥ ሲባል ፎቶግራፍ ለማንሳት አከራዩ ወደ ቤትዎ እንዲገባ በሕግ መብት አልተሰጠውም፡፡
አከራዩ መብት የሌለው በመሆኑ ወደ ቤትዎ እንዳይገባ ለመከልከል ይችላሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ወደ ቤትዎ እንዲገባ የሚፈቅዱ ከሆነ ፎቶግራፍ የሚነሳው የትኛው እንደሆነና ፎቶግራፉ ለምን አገልግሎት እንደሚውል ስምምነት ማድረግ ይችላሉ፡፡ ፎቶግራፍ ከሚያነሳው ሰው ጋር አከራዩ ወይም የሪል ኤስቴቱ ወኪል አብረውት እንዲገኙ ጠንካራ አቋም መያዝ ይኖርብዎታል፡፡
ንብረቶችዎን የሚያሳዩት ፎቶዎች የስርቆት አደጋ ሊያስከትሉብዎ እንደሚችሉ ጥርጣሬ ካለዎት ፎቶግራፍ ከመነሳቱ ቢት ውድ ዋጋ ያላቸውን ንብረቶችዎን መሸፈን ወይም ማንሳት ያስፈልጋል፡፡
የእርስዎን ወይም የቤተሰብዎን አባል በግልጽ በማሳየት ፎቶዎቹ የግል ሕይወትዎን መከበርና መጠበቅ ይጥሳሉ ብላው ካሰቡ ምክር ለመጠየቅ የAustralian Information Commissionerበ1300 363 992ላይ ይደውሉ፡፡
መቼ እና በምን ያህል ጊዜ ልዩነት ወደ ቤትዎ መምጣት እንደሚችሉ ከአከራይዎ ወይም ከወኪሉ ጋር ስምምነት ማድረግ ሊሞክሩ ይችላሉ፡፡ ስምምነቱን በጽሁፍ ማድረግና በእርስዎና በአከራዩ ወይም በወኪሉ መፈረሙን ማረጋገጥ ይኖርብዎታል፡፡
ስምምነቱ የሚከተሉትን ሁኔታዎች ሊያካትት ይችላል፡
የእርስዎን በቤትዎ ውስጥ በሰላምና በጸጥታ የመኖር መብት በማወኩ ምክንያት አከራይዎ ወይም ወኪሉ ወደ ቤትዎ የገቡት ምክንያታዊ ባልሆነ ሁኔታ ነው ብለው ካሰቡ የመግባታቸውን ሁኔታ ለመገደብ እርምጃ መውሰድ ይችላሉ፡፡
አከራይዎ ወይም ወኪሉ በቂ የማስታወቂያ ጊዜ ካልሰጡዎት፣ ‘ምክንያታዊነት የለውም’ ተብሎ ሊቆጠር በሚችል ሁኔታ ቤቱን ለሰዎች በተደጋጋሚ የሚያሳዩ ከሆነ ወይም ቤቱ ውስጥ ለረጅም ሰዓት ከቆዩ ነው፡፡
አከራይዎ ምክንያታዊነት የለውም ብለው ካሰቡ የዕግድ ትዕዛዝ ለማግኘት ለVCAT ለማመልከት ይችላሉ፡፡ ምን እንደተፈጸመ ማስረጃ ማቅረብ ያስፈልግዎታል፡፡ ለምሣሌ ቤቱን ለሰዎች ያሳየበትን ቀንና ሰዓት እንዲሁም በእያንዳንዱ ጉብኝት ወቅት ምን ያህል ሰዓት እንደቆዩ ጽፎ መያዝ ይቻላል፡፡
የዕግድ ትዕዛዝ ለማግኘት የሚቀርቡ ማመልከቻዎች ከሌሎች አስቸኳይ ማመልከቻዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሲሆን ችሎቱም በጥቂት ቀናት ውስጥ ሊሰየም ይችላል፡፡ ችሎት የሚሰየምበት ቀን ተወስኖ እንደሆነ ለማወቅ ማመልከቻዎን ካስገቡ ከአንድ ቀን በኋላ ለVCAT ስልክ ደውሎ መጠየቅ ጥሩ ነው፡፡ ያልተወሰነ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን መልሰው ይደውሉ፡፡ እርስዎ በቀጠሮው ቀን ካልቀረቡ VCAT ለአከራዩ ሊወስንለት ይችላል፡፡
አከራዩ በቤትዎ ውስጥ በሰላምና በጸጥታ እንዲኖሩ ለማድረግ ተገቢውን እርምጃ ካልወሰደ በእርሱ በኩል ግዴታን ያለመወጣት ወይም መጣስ ስለሆነካሣ እንዲከፈልዎት ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ቤቱ ውስጥ በገቡበት ወቅት ንብረቶችዎ ተሰርቀው ወይም ጉዳት ደርሶባቸው ከሆነ ካሣ እንዲከፈልዎት ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡
አያስፈልግዎትም፡፡ ንብረቱ ተሸጦ ከሆነ የኪራይ ውልዎ ቀድሞ በነበረው ደንብና ሁኔታ በመደበኛነት (የሚከፍሉት የኪራይ ክፍያ መጠንን፣ እንዴትና መቼ እንደሚከፍሉ፣ እና የውሉ የተወሰነ ጊዜ መቼ እንደሚያልቅ የሚሉትን ጨምሮ) ይቀጥላል፡፡ አዲስ የሚለወጥ ነገር ቢኖር አዲሱ ባለቤት የቀድሞውን አከራይ መብትና ግዴታዎች መውረሱ ነው፡፡ የአዲሱ የንብረቱ ባለቤት ስም ማን እንደሆነ የሚገልጽ ደብዳቤ ሊደርስዎት ይገባል፡፡
ንብረቱ በሚሸጥበት ወቅት አዲሱና የቀድሞው ባለቤት ለResidential Tenancies Bond Authority (RTBA)የውሉ ዘመን እስከሚያበቃ ድረስ እርስዎ ያስያዙት መያዣ RTBA ዘንድ እንደሚቆይ ማስታወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ የአከራይዎ ሥም በመያዣ ማስገቢያው ቅጽላይ ተጠቅሶ ከሆነ የአዲሱን አከራይ ሥም የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ከRTBA ማግኘት ይገባዎታል፡፡ የሪል እስቴት ወኪል ስም በ የመያዣ ገንዘብ መመዝገብያ ቅጽ (Bond Lodgement form) ፣ ምንም ነገር አይለወጥም።
ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።
[disclaimer-rta-amharic]
ሕጉ
Residential Tenancies Act 1997 (AustLII website)
section 67 – quiet enjoyment
section 70 – locks
section 70A – locks for properties subject to intervention orders/notices
section 71 – applying to VCAT to change locks without consent
section 85 – entry of rented premises
section 86 – grounds for entry
section 87 – manner of entry
section 88 – what must be in notice of entry?
section 89 – duty to allow entry if requirements met
section 90 – applying to VCAT for compensation if damage is caused during entry
section 91 – applying to VCAT for a restraining order
section 91A – offence to enter premises without meeting requirements
section 259 – notice to vacate for sale
Higgerson v Ricco (Residential Tenancies) [2014] VCAT 1214
resources
for sale selling sold (print) [pdf, 245kb]
ተዛማጅ ገፆች
የግል ሕይወት መከበርና መጠበቅ እና ወደ ቤት የመግባት ሁኔታ
አከራዮች ሃላፊነታቸውን ሲጥሱ
ቤቱን እንዲለቁ ስለሚሰጥ ማስታወቂያ
ቅሬታ ስለማቅረብ
ለተከራዮች ስለሚከፈል ካሣ
ቤቱን ለቀው መሄድ ሲፈልጉ
የኪራይ ውልዎን ስለማፍረስ
የኪራይ ግንኙነት ስለመጀመር
ሸንጎው (VCAT)