በመንግሥት መኖሪያ ቤት ለተሰጠ ውሳኔ አቤቱታ ስለማቅረብ - Tenants Victoria

በመንግሥት መኖሪያ ቤት ለተሰጠ ውሳኔ አቤቱታ ስለማቅረብ

በ Director of Housing* የተሰጠ ውሳኔ ላይ ካልተስማሙ ውሳኔው እንደገና እንዲታይ የጥያቄ አቤቱታ ማቅረብ ይችላሉ።

አቤቱታ ማቅረብ የሚችሉት:

 • ለመንግሥት መኖሪያ ቤት አመልክተው ከሆነ፣ ወይም
 • ለማስያዣ ገንዘብ እርዳታ አመልክተው ከሆነ፣ ወይም
 • በአሁን ጊዜ የመንግሥት መኖሪያ ቤ ንብረት ተከራይተው ከሆነ ነው።

በሚከተሉት ውሳኔዎች ላይ አቤቱታ ማቅረብ ይችላሉ:

 • ለመንግሥት መኖሪያ ቤት ፍቃድ ማግኘት
 • በቅድሚያ ለመኖሪያ ቤት ምደባ ፍቃድ ማግኘት
 • የመኖሪያ ቤት ምደባ ወይም አቅርቦት
 • ወደሌላ የመኖሪያ ቤት ማስገባት ወይም ቅያሬ
 • በጋራ ስምምነት መቀያየር
 • ለተለቀቀ የመኖሪያ ቤት ማመልከቻ
 • የዋጋ ቅናሽ ስሌት ይህም የርስዎን ቅናሽ ዋጋ መሰረዝ ያካተተ ወይም ወደኋላ ተመልሶ የዋጋ ቅናሽ ስሌት
 • Bond Loan Scheme
 • ለማስያዣ ገንዘብ እርዳታ ፍቃድ ማግኘት
 • ለመኪና ማቆሚያ ቦታ ምደባ
 • ለተንቀሳቃሽ ክፍሎች
 • ለየት ላለ የጥገና ሥራ ጥያቄ

በ Victorian Civil and Administrative Tribunal (VCAT) በኩል የተደረገው ድርድር በመኖሪያ ቤት ጉዳይ አቤቱታ ሂደት ላይ ግምት ውስጥ መግባት አይችልም።

በእነዚህ ጉዳዮች ላይ የሚካተት:

 • ውዝፍ የቤት ኪራይ
 • Notices to Vacate እና Possession Orders
 • ለጥገና እና ለንብረት እድሳት ጥያቄ
 • የተከራይ ሃላፊነት ክፍያዎች

ለውሳኔው እንዴ አቤቱታ ማቅረብ እንደሚቻል

እርምጃ 1. የአካባቢዎ የመንግሥት መኖሪያ ቤት ቢሮ

ስለሚኖርዎ አሳሳቢ ጉዳዮች ከአካባቢዎ መኖሪያ ቤት ቢሮ ጋር መነጋገር። በውሳኔው ላይ አሁንም ደስተኛ ካልሆኑ አቤቱታ ማስገባት ይችላሉ።

እርምጃ 2. የእርስዎን አቤቱታ ስለማቅረብ

በተቻለ ፍጥነት የአቤቱታ ማመልከቻዎን መጀመሩ በጣም ጥሩ ነው። አቤቱታ ለማቅረብ ክፍያ እንደሌለበትና ጉዳይዎ በሚስጢር ሲጠበቅ፤ ነገር ግን በጽሁፍ አድርጎ ማቅረብ ይኖርብዎታል።

በውሳኔ ላይ አቤቱታ ለማቅረብ Housing Appeal Application Form የሚለውን ቅጽ ሞልቶ ከአጠናቀቁ በኋላ ለHousing Appeals Office ማስገባት አለብዎት። በሳኔው ላይ ያለዎትን ተቃውሞና ለምን የሚለውን በአቤቱታው ላይ መግለጽ አለብዎት። ለእርስዎ ጉዳይ የሚደግፉ ማንኛውም ሰነድ ቅጅውን አብሮ ማያያዝ ያስፈልግዎታል።

ለርስዎ ማመልከቻ ለማጠናቀቅ የሆነ ጥያቄ ወይም እርዳታ ከፈለጉ ለ Housing Appeals Office በስልክ  03 9096 7426 ወይም  1800 807 702 ለገጠር ነዋሪዎች (በነጻ ጥሪ) አድርገው ማነጋገር ወይም ምክር ለማግኘት የ Tenants Union/Tenants Victoria በስልክ 1800 068 860 ማነጋገር ነው።

እርምጃ 3. ከመኖሪያ ቤት አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ ምላሽ

የአቤቱታ ማመልከቻዎን አንዴ ካስገቡ በኋላ ስለመድረሱ የሚገልጽ ደብዳቤ ከHousing Appeals Office ይደርስዎታል።

በማመልከቻዎ ላይ ባቀረቡት መረጃ መሰረት በመጀመሪያ የእርስዎ አቤቱታ በአካባቢዎ ባሉ ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት ሰራተኞች በኩል ምርመራ ይደረጋል።

የእርስዎ አቤቱታ በደረሰ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ የዚህ የመጀመሪያ ግምገማ ውጤት እንዴት እንደሆነ ምክር ለመስጠት የመኖሪያ ቤት አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ ያነጋግርዎታል።

እርምጃ 4. የመኖሪያ ቤት አቤቱታ ሥራ አስኪያጅ

የመጀመሪያው ውሳኔ በመኖሪያ ቤት አገልግሎት ሥራ አስኪያ በኩል ካልተቀየረ፤ ከዚያም በኋላ የመኖሪያ ቤት ዳሬክተር ፖሊሲ/ Director of Housing’s policy እና የሥራ አፈጻጸም በትክክለኛ መንገድ ስለመካሄዱ ለማጣራት ወደ የመኖሪያ ቤት አቤቱታ ሥራ አስኪያጅ ይላካል።

ስላቀረቡት አቤቱታ ለመነጋገር የይግባኝ ሥራ አስኪያጅ በተለፎን ወይም በአካል ቃለመጠይቅ ለማካሄድ ቀጠሮ ሊያቀናጅልዎ ይችላል። በዚህ ቃለመጠይቅ ላይ የእርስዎን ሁኔታ ለመግለጽ እና ተጨማሪ መረጃ ለማቅረብ ያስችልዎታል። በማንኛውም ቃለመጠይቅ ጊዜ አስተርጓሚ እንዲቀርብ መጠየቅ ይችላሉ።

የአቤቱታ ማመልከቻዎን ካስገቡ በኋላ በአንድ ወር ውስጥ የይግባኝ ሥራ አስኪያጅ ካላነጋገርዎት፤ ለ Housing Appeals Office መደወል አለብዎ።

የርስዎ አቤቱታ በ Housing Appeals Office በኩል ከተጣራ በኋላ ውጤቱን ለማሳወቅ በደብዳቤ ይላክልዎታል።

እርምጃ 5. አቤቱታ ሰሚ ወይም Human Rights & Equal Opportunity Commission

ባቀረቡት የመኖሪያ ቤት አቤቱታ ውጤት ደስተኛ ካልሆኑ ለOmbudsman Victoria ማነጋገር ይችላሉ ወይም በርስዎ ላይ አድልዎ ተደርጓል ብለው ካመኑ የ Human Rights and Equal Opportunity Commission. ማነጋገር ይችላሉ።

አቤቱታ ሰሚ

በ Director of Housing በኩል ስለተካሄደ ውሳኔና አስተዳደራዊ እርምጃ ለሚቀርብ አቤቱታ የOmbudsman of Victoria ሊያጣራው ሲችል፤ እንዲሁም ስለሠራተኛ ባህሪና ተግባር በተመለከተ ለአቤቱታ ሰሚ ማመልከት ያለክፍያ በነጻ ነው።

የአቤቱታ ሰሚው የራሱን ሃሳብ እንደ ምክር ለመኖሪያ ቤት ዳሬክተር ማቅረብ ይችላል።

Ombudsman Victoria በስልክ  03 9613 6222 ወይም  1800 806 314 ለገጠር ነዋሪዎች (በነጻ ጥሪ) አድርገው ለማነጋገር ይችላሉ።

Equal Opportunity & Human Rights Commission

በሰዎች ላይ አድልዎና የማስፈራራት ጉዳዮችን በተዛመደ የ Victorian Equal Opportunity and Human Rights Commission እርዳታ ያቀርብላቸዋል።

ኮሚሽኑ የቀረበውን አቤቱታ በጋራ ስምምነት መፍትሄ እንዲያገኝ ይረዳል። ያለክፍያ በነጻና ሚስጢራዊ ለሆነ ምክር ለማግኘት ለኮሚሽኑ በስልክ 1300 292 153 መደወል።

*የመንግሥት አካል የሆነው የህዝብ መኖሪያ ቤቶችን የሚያስተዳድር መስሪያ ቤት ቀደም ሲል ብዛት ያለው ስም ይጠቀም ነበር ከነዚህ መካከል the Housing Commission, Department of Housing and Office of Housing ናቸው። በአሁን ጊዜ Housing and Community Building Division of the Department of Human Services ተብሎ ይጠራል። ይህንን አገልግሎት በሚገባ ለመግለጽ ሲባል የ name Director of Housing የሚለውን ስም Tenants Union/Tenants Victoria እንደ አማራጭ ይጠቀማል።
እባክዎ ያስተውሉ፤ በአሁን ጊዜ የአካባቢዎ መኖሪያ ቤት ቢሮ በ Department of Human Services ውስጥ ሊገኝ ይችላል።

ካለፈው ገጽ የቀጠለ

 ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

ከዚህ ጋር የተዛመዱ ገጾች

ለመንግሥት መኖሪያ: የጥገና ወጪን ስለማስወገድ
 

በበለጠ እርዳታ ይፈለጋልን?

ተጨማሪ መረጃ ወይም እርዳታ ካስፈለግዎት እባክዎ እኛን ያነጋግሩ።


Appealing a public housing decision | Amharic | June 2012

እኛን ያግኙን

ለተከራዮች ምክር (advice for tenants)
እኛን ያግኙን (contact us)

የቪክቶርያ ተከረዮች | የተከራዮች የድጋፍ መስመር 03 9416 2577 | tenantsvic.org.au
የቪክቶርያ ተከራዮች የቪክተርያ መንግስት ድጋፍ ዕውቅና ይሰጡታል፡፡

Tenants Victoria acknowledges the support of the Victorian Government.