ለመንግሥት መኖሪያ: የጥገና ወጪን ስለማስወገድ - Tenants Victoria

ለመንግሥት መኖሪያ: የጥገና ወጪን ስለማስወገድ

የጥገና ክፍያዎች ምንድ ናቸው?

ከመንግሥት መኖሪያ ቤት በሚለቁበት ጊዜ በንብረቱ ላይ ለተበላሸ፣ ለጥገና ወይም ለጽዳት የሚሆን ክፍያ ገንዘብ ካስፈለገ የ Director of Housing* ሊጠይቅዎ ይችላል።

እነዚህ ክፍያዎች ብዙጊዜ መጠገኛ ክፍያ ተብለው ይጠራሉ፣ ተከራዩ የሚከፍላቸው የጥገና ክፍያዎች (MCAT)፣ የመልቀቂያ ማስጠገኛ ክፍያ ወይም የተከራይ ሃላፊነት (TR) ክፍያ ይባላል።

በ Victorian Civil & Administrative Tribunal (VCAT ልዩ ፍርድ ቤት በኩል መክፈል አለብዎ የሚል ትእዛዝ ካልተሰጠ በስተቀር እነዚህን ክፍያዎች መክፈል አይኖርብዎትም።

ህጉ ምን ይላል

በቪክቶሪያ የተከራይና አከራይ ህግ መሰረት ሁሉም ተከራዮች የተከራዩትን ንብረት በንጽህና መጠበቅ እና በንብረቱ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አስፈላጊውን እርምጃ ስለመወሰዱ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል። እነዚህን ተግባራት ካሟሉ፤ ምንም ክፍያ እንዳይከፍሉ ልዩ ፍርድ ቤቱ/ VCAT መወሰን አለበት።

ይሁን እንጂ ከነዚህ ግዴታዎች አንዱን ከጣሱ የ Director of Housing (የርስዎ ባለንብረት) ህጉን በመጣስዎ ለደረሰ ማንኛውም ጥፋት ወይም ወጪ በሙሉ የካሳ ጥያቄ ማቅረብ ይችላል። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ‘የDirector of Housing ጥያቄ ካቀረበ’ የሚለውን ወረቀት ማየት።

የማስጠገኛ ክፍያን እንዴት ማስወገድ ይቻላል

የተከራይና አከራይ ውል በሚያልቅበት ጊዜ የማስጠገኛ ክፍያን ለማስወገድ ተከራይተው በሚኖሩበት ጊዜ እና ከዚያ በኋላ መከተል ያለብዎ የተለያዩ ቀለል ያሉ እርምጃዎች አሉ።

በተከራይና አካራይ ውል ጊዜ

በንብረቱ ላይ አስፈላጊ ለሆነ ማንኛውም ጥገና የመኖሪያ ቤት ዳሬክተር እንዲያውቅ በተቻለ ፍጥነት ሪፖርት ስለማድረግዎ ማረጋግጡ። በበለጠ መረጃ ለማግኘት በእኛ የመንግሥት ቤት ጥገና የሚለውን እውነታ ጽሁፍ ወረቀት ማየት።

በንብረቱ ላይ ማንኛውም አይነት ብልሽት ካለም ይህንን በተቻለ ፍጥነት ለ Director of Housing ሪፖርት ማድረግ አለብዎት።

የ Director of Housing ለተፈጠረው ማንኛውም ጉዳት የርስዎ ሃላፊነት ነው ብሎ ካመነበት፤ ለተፈጠረው ጉዳት ማስጠገኛ የሚከፈል ወጪን እንዲያካሂዱ ከልዩ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝን ሊጠይቁ ይችላሉ። ያስተውሉ፡ ማንኛውንም ጉዳት ለማስወገድ አስፈላጊውን እርምጃ ባልወሰዱበት ሁኔታ ብቻ የርስዎ ሃላፊነት ሊሆን ይችላል። ይህ ማለት ለምሳሌ፡ ሌላ ሰው ቤትዎን ሰብሮ ሲገባ ወይም በሃይለኛ ዝናብ ወይም ነፋስ ሳቢያ ቤትዎ ላይ ጉዳት ለሚደርስው ጉዳት የርስዎ ሃላፊነት አይደለም።

ለማስጠገኛ ጥያቄ ከDirector of Housing ከደረስዎ ምክር ለማግኘት የTenants Union/Tenants Victoria በስልክ 1800 068 860 ደውለው ያነጋግሩ። የ Tenants Union/Tenants Victoria ያለክፍያ በነጻ ሚስጢራዊ የሆነ ምክር ለተከራዮች ይሰጣል፤ የመንግሥት ቤት ተከራዮችንም ያካትታል።

ከቤቱ በሚለቁበት ጊዜ

ስለርስዎ ንብረት የሁኔታ መግለጫ ሪፖርት መኖር አለበት። ይህ ሪፖርት እርስዎ ወደ ቤቱ ሲገቡ የነበረውን ሁኔታ ይገልጻል። የንብረት ሁኔታ መግለጫ ሪፖርት ከሌለዎት ቅጂውን ሊሰጥዎት ከቻሉ ለአካባቢዎ የመኖሪያ ቤት ቢሮ መጠየቅ። ቀደም ሲል በሪፖርት መግለጫው ላይ ለተመዘገበ ወይም ወደ ቤት ሲገቡ ለነበረ ጉዳት በሃላፊነት ሊጠየቁ አይገባም።

ቤቱን በሚለቁበት ጊዜ የርስዎ ሃላፊነት መስሎ የታየዎትን ማንኛውም የጥገና ሥራ ማካሄድና ንብረቱን ማጽዳት አለብዎ። የአትክልት ቦታ ካለ ንጽህናው የተጠበቀ ስለመሆኑ አይዘንጉ። ማንኛውም ጥገና ጥሩ የጥገና ሙያ ባለው ሰው መካሄድ አለበት። ይህ ማለት በተገቢ ደረጃ መጠን በሚገባ መጠገን እንዳለበት። በአብዛኛው ጊዜ በባለሙያ የጽዳት፣ የምንጣፍ በስቲም/እንፋሎት ጽዳት ሰራተኛ ማካሄዱ አይስፈልግ ይሆናል። ነገር ግን ንብረቱ ተገቢነት ባለው የጽዳት ደረጃ መተው አለበት።

የንብረቱን ቁልፎች ከመመለስዎ በፊት ሁሉም ነገር ተካሂዶ ከሆነ ለማረጋገጥ የመጨረሻ ፍተሻ ማካሄድ። ምናልባት ክርክር አለመግባባት ከተፈጠረ ቤቱን በሚለቁበት ጊዜ ስለ ንብረት ሁኔታ ሊመሰክር የሚችል ጓደኛ ወይም የሆነ ሰው ይዞ መሄዱ የሚደገፍ ሃሳብ ነው። እንዲሁም ቤቱን በሚለቁበት ጊዜ የንብረቱን ይዘት የሚያሳይ ፎቶግራፍ ወይም በቪድዮ መቅረጽ ይችላሉ።

አንዴ ከነበሩበት ቤት ከወጡ፤ በ Director of Housing ፍተሻ ያካሂዳል። የተፈጠረው ጉዳት ወይም ጥገናዎች ላይ የርስዎ ሃላፊነት እንደሆነ በDirector of Housing በኩል ከታመነበት፤ በርስዎ ላይ ተገቢ የሆነ ጥያቄ ማቅረብ አለባቸው።

የ Director of Housing ጥይቄ ቅሬታ ካቀረበስ

በ Director of Housing በኩል የሚቀርብ የማስጠገኛ ጥያቄ ማካተት ያለበት፤ በንብረቱ ላይ ምን የብልሽት ስህተት እናዳለ ትክክለኛ ዝርዝር መግለጫ እና ችግሩን ለማስጠገን ምን ያህል እንደሚያስወጣ መግለጽ አለበት።

በጥያቄው ላይ ሁሉንም ዝርዝር መግለጫ ካልተካተተ በርስዎ ላይ ስለቀረበ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥዎት በአካባቢዎ መኖሪያ ቤት ቢሮ መጠየቅ አለብዎት። ለሥራ ወይም ለጥገና ትእዛዝ ወይም ለተጠናቀቀ ሥራ የሂሳብ መጠየቂያ ደረሰኝ ሊኖር ይገባል።

ለጥገና የወጣ ክፍያ ጥያቄ በ Director of Housing በኩል ከደረስዎ ምንም እንኳን በአሁኑ ጊዜ የመንግሥት መኖሪያ ቤት ተከራይ ባይሆኑም ጉዳዩን ችላ አለማለት በጣም ያስፈልጋል። ምንም እርምጃ ካልወሰዱ ለመኖሪያ ቤቶች ዳሬሪክተር የሚከፍሉት እዳ እንዳለብዎ የሚገልጽ ትእዛዝ በVictorian Civil and Administrative Tribunal (VCAT) በኩል ይሰጣል። እዳው ካልተከፈለ፣ ይህ እዳ ለወደፊቱ የመንግሥት መኖሪያ ቤት ለማግኘት ሊያስከለክልዎ ይችላል።

ለክፍያው የርስዎ ሃላፊነት መሆ ወይም አለመሆን እርግጠኛ ካልሆኑ ከTenants Union/Tenants Victoria በስልክ 1800 068 860 ደውሎ ምክር ማግኘት አለብዎ።

ለሙሉው ክፍያ ወይም ከፊል ክፍያ ላይ የርስዎ ሃላፊነት ስለመሆኑ ካላመኑበት ከ Director of Housing ለመደራደር መሞከር አለብዎ። አነስተኛ ክፍያ ለማካሄድ ወይም የተወሰነ መጠን ቀስ በቀስ ከፍሎ ለመጨረስ ስምምነት ላይ ሊደርሱ ይችላሉ። እንደ ተከራይ መጠን ግዴታን አልጣስኩም ብለው ካመኑ፤ ክፍያውን ለማካሄድ አለመስማማት። የማካካሻ ክፍያ ለማግኘት የThe Director of Housing ለ VCAT ማመልከት አለበት።

ያስታውሱ፡ ወደ ልዩ ፍርድ ቤት VCAT ሂዶ ለጥገና ክፍያ ክስ በመከራከር ምንም የሚያጡት ነገር የለም። ለካሳ ክፍያ ጥያቄ የሚከራከሩ ተከራዮች ብዙጊዜ ያሸንፋሉ።

 ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።


 

ከዚህ ጋር የተዛመዱ ገጾች

ለማካካሻ ክፍያ ጥያቄ ስለመከራከር
በቪክቶሪያ ሲቪልና አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት
የመንግሥት መኖሪያ ቤት ጥገና

በበለጠ እርዳታ ይፈለጋልን?

ተጨማሪ መረጃ ወይም እርዳታ ካስፈለግዎት እባክዎ እኛን ያነጋግሩ።


Avoiding public housing maintenance charges | Amharic | June 2012

እኛን ያግኙን

ለተከራዮች ምክር (advice for tenants)
እኛን ያግኙን (contact us)

የቪክቶርያ ተከረዮች | የተከራዮች የድጋፍ መስመር 03 9416 2577 | tenantsvic.org.au
የቪክቶርያ ተከራዮች የቪክተርያ መንግስት ድጋፍ ዕውቅና ይሰጡታል፡፡

Tenants Victoria acknowledges the support of the Victorian Government.