ኮንትራትን ስለማቋረጥ - Tenants Victoria

  ኮንትራትን ስለማቋረጥ

  ለተወሰነ የጊዜ ገደብ የተከራይና አከራይ ውል ስምምነት አድርገው ከሆነ (ብዙጊዜ ኮንትራት ይባላል) እና የተወሰነው ጊዜ ሳይደርስ ከቤት መልቀቅ ከፈለጉ፤ ከሚከተሉት መንገዶች በአንደኛው ኮንትራትዎን ማቆም ይችሉ ይሆናል። አንዳንድ የኮንትራት ማቆሚያ ዘዴዎች ሊያስከፍሉ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ማድረግ አለብዎ።

  ይህ ገጽ

  የጋራ ስምምነት
  ባለንብረቱ ግዴታውን በሚጥስበት ጊዜ
  ለሌላ ማስተላለፍ
  በችግር ላይ
  ንብረትን ስለማስረከብ
  ወጪ ክፍያ
  ወጪዎችን ስለመቆጣጠር

  የጋራ ስምምነት

  ማንኛውም የተከራይና አከራይ ውል ስምምነት በተከራይና አከራይ መካከል በሚደረግ ስምምነት ሊቋረጥ ይችላል። ለስምምነቱ ጽሁፍ ማግኘት እንዳለብዎ በጥብቅ እያሳሰብን፤ ይህም ኮንትራቱ ስለተቋረጠ ለማንኛውም ተጨማሪ ወጪ ወይም የካሳ ክፍያ ማካሄድ እንደለለብዎ በጽሁፉ መግለጽ ይኖርበታል። እርስዎና ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካይ በስምምነቱ ላይ መፈረም አለባችሁ። ቅጂውን እንዳስቀመጡ ያረጋግጡ።

  ባለንብረቱ ግዴታውን በሚጥስበት ጊዜ

  Residential Tenancies Act 1997አንቀጽ ህግ መሰረት የርስዎ ባለንብረት ያለበትን ‘ተግባር/ግዴታ’ ካላሟላ፤ የርስዎን የተከራይ አከራይ ውል ስምምነት ቀደም ብሎ ማቆም ይችሉ ይሆናል። ይህ ተግባራዊ የሚሆን ባለንብረቱ:

  • ወደ ቤቱ እንደሚገቡ እየታወቀ ንብረቱ በተገቢው ንጽህና ላይ ስለመሆኑ እርግጠኛ አለመሆን
  • በንብረቱ ላይ ‘በጥሩ አስደሳች’ ሱኔታ ለመኖር እርግጠኛ አለመሆን
  • ንብረቱን በጥሩ ጥገና አለመጠበቅ
  • የውጭ መስኮቶችና በሮችን ደህንነት ለመጠበቅ መቆለፊያ አለማቅረብ ወይም መቆለፊያውን ሲቀይሩ ቁልፍ አለመስጠት
  • ለተበላሸ የውሀ ቧንቧ መሳሪያ ጥራቱ አንደኛ-ደረጃ በሆነ እቃ አለመቀየር

  ተከራይና አከራይ ውል ስምምነት ከተወሰነው ጊዜ በፊት ከመቋረጡ በፊት ሊወስዷቸው የሚገቡ አንዳንድ እርምጃዎች አሉ።

  1. የመጀመሪያ እርምጃ፡ ችግሩ (እና የመሳሪያ ካሳ ክፍያ ተገቢ ከሆነ) በ14 ቀናት ውስጥ መጠገን እንዳለበት Breach of Duty Notice ማሳሰቢያ ለርስዎ ባለንብረት መላክ ነው።
  2. ባለንብረቱ ይህንን ካላደረገ የ Compliance Order ትእዛዝ እንዲሰጥ ለ Victorian Civil and Administrative Tribunal ልዩ ፍርድ ቤት ማመልከት ይቻላል።
  3. በቀረበ የ Compliance Order ትእዛዝ የማይከተል ከሆነ በ14 ቀናት ውስጥ ለመልቀቅ እንደፈለጉ የNotice of Intention to Vacate መላክ ይችላሉ።
  4.  እንዲሁም ለመልቀቅ እንደፈለጉ የ14 ቀናት ማስጠንቀቂያ መላክ ይችላሉ። በተመሳሳይ ግዴታ ከመጣስ በፊት ሁለት ጊዜ የ Breach of Duty Notice ማስጠንቀቂያ ከላኩላቸውና ባለንብረቱ ግዴታውን ለሶስተኛ ጊዜ ጣሰ ማለት ነው።

  ለሌላ ማስተላለፍ

  የኮንትራት ውልዎን ከመጣስ ፋንታ የርስዎን የተከራይና አከራይ ስምምነት ውል ለሌላ ተከራይ ማስተላለፍ ወይም ‘መመደብ’ የቀለለ ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ የባለንብረት ስምምነት፣ የተከራይና አከራይ ውል ማደስና ለማስያዣ ገንዘብ ማስተላለፍ እስከሚቀናጅ ድረስ ለሌላ ተከራይ መስጠት ስለማይቻል ይህ አማራጭ ሁልጊዜ ቀላል አይደለም። በተጨማሪም ወደሌላ ተከራይ ለማስተላልፍ ባለንብረቱ የጹሁፍ ስምምነት ለማዘጋጀት ያስከፍላል፤ ነገር ግን ለአዲስ ተከራይ አዲስ የተከራይና አከራይ ውል ለመፍጠር ክፍያ ማካሄድ አይችሉም።

  በችግር ላይ

  የተወሰነው ጊዜ ገደብ ውል ከመድረሱ በፊት ያልተጠበቀ ነገር ከተፈጠረና በንብረቱ ላይ ለመቆየት በጣም አስቸጋሪ ከሆነ የውሉ ጊዜ ገደብ ተቀንሶ ያለዎት ስምምነት ውል እንዲያበቃ ለ Victorian Civil and Administrative Tribunal ልዩ ፍርድ ቤት ማመልከት ይችላሉ። ልዩ ፍርድ ቤቱ ጉዳይዎን በተቻለ ፍጥነት እንዲያየው መጠየቅ አለብዎት። ጉዳይዎ በፍርድ ችሎት እስከሚታይ ድረስ ግን የተለመደውን የቤት ኪራይ ክፍያ ማቋረጥ የለብዎም። በችግር ሳቢያ ለማመልከት ካቀዱ፣ ከመውጣትዎ በፊት ማመልከት አለብዎ።

  በችግር ሳቢያ ለማመልከት የሚከተለውን ለልዩ ፍርድ ቤቱ ማረጋገጥ አለብዎ:

  • በርስዎ ሁኔታ ላይ ያልተጠበቀ ለውጥ ሲከሰት (ለምሳሌ፡ ከሥራ መባረር) እና የተከራይና አከራይ ውል ከቀጠለ በከፍተኛ ችግር እንደሚሰቃዩ፤ እና
  • የተከራይና አከራይ ውል ስምምነት ጊዜ ካልቆመ ሊያጋጥምዎት የሚችለው ችግር ከባለንብረቱ ችግር የበለጠ እና የሚሰቃዩ ከሆነ

  በችግር ሳቢያ የቤት ኪራይ ውሉን ካቋረጡ አሁንም ለባለንብረቱ መካካሻ ክፍያ ሊሰጡ ይችላሉ።

  ከባድ ችግርና በቤተሰብ ሁከት

  በቤተሰብ ሁከት የእገዳ ትእዛዝ በኩል ‘ደህንነትዎ የሚጠበቅ ሰው’ ከሆኑና ለርስዎ ወይም ልጆችዎ ደህንነት ሲባል መልቀቅ ካለብዎ ታዲያ የተወሰነው የኪራይ ውል ጊዜ ገደብ እንዲቀነስና የተከራይና አከራይ ስምምነት ውል መቆም እንዲችል ለልዩ ፍርድ ቤት ትእዛዝ እንዲሰጥበት ማመልከት ይችላሉ።

  በቤተሰብ ሁከት የእገዳ ትእዛዝ ምክንያት ከተከራዩት መኖሪያ ቤት ከወጡ ታዲያ የተወሰነው ኪራይ ውል ጊዜ ገደብ ቀደም ብሎ እንዲቆምና እንዲሁም ባለዎት ችግር ሳቢያ የኪራይ ኮንትራት ስምምነት ውሉን ለማስቆም እንዲቻል ለልዩ ፍርድ ቤት ትእዛዝ እንዲሰጥበት ማመልከት መብትዎ ነው።

  ንብረትን ስለማስረከብ

  ከዚህ በላይ ያሉት የኮንትራት ማቆም ዘዴዎች ስለሚኖርዎ ለርስዎ አማራጭ ከሆነ ታዲያ ንብረትን በማስረከብ ለተወሰነው ጊዜ ገደብ ያለውን የኪራይ ኩንትራት ስምምነት ውል ቀደም ብሎ ማቆምና ከንብረት መውጣት ይቻላል። (ይህም የ Notice of Intention to Vacate) ማስጠንቀቂያ መስጠትና ቁልፎቹን በመመለስ ቤቱን መልቀቅ።

  ወጪ ክፍያ

  በችግር ላይ እያሉ ቤቱን በማስረከብዎ ሳቢያ የኮንትራት ውል መጣስ ዋጋው ውድ ሊሆን ይችላል።

  የኮንትራት ውል በመጣስዎ ለወጣ ማንኛውም ወጪ ባለንብረቱ የካሳ ክፍያ መጠየቅ ይችላል።

  መክፈል ባለብዎ ክፍያ/ወጪ ላይ የሚካተት:

  • ለሌላ የማከራያ ክፍያ (ብዙጊዜ የአንድ ወይም የሁለት ሳምንት የቤት ኪራይ)። የንብረት ተወካይ ለባለንብረቱ በሚያስከፍለው መሰረት ይህ ክፍያ መወሰን አለበት። ታዲያ የተከፈለበትን ደረሰኝ ቅጂ መጠየቁ አስፈላጊ ነው።
  • ለማስታወቂያ ተገቢ የሆነ ወጪ ክፍያ
  • ሌላ አዲስ ተከራይ እስኪገባ ድረስ የቤት ኪራይ ክፍያ ወይም የተወሰነው ጊዜ ገደብ እስከሚያልቅ መክፈል (ቀድሞ ለተከሰተው)

  ባለንብረቱ ወይም ተወካይ ድርጅቱ ለርስዎ መናገር የማይኖርባቸው ነገር ቢኖር በየጊዜው ለሌላ ተከራይ ክፍያ መክፈል እንዳለብዎ፤ ይህ ማለት እርስዎ መክፈል ያለብዎ የተወሰነው ጊዜ ገደብ ውል እስካለቀ ድረስ ብቻ ይሆናል። ለምሳሌ፡ በ12 ወር የተከራይና አከራይ ውል ስምምነት ላይ ከ7 ወር በኋላ ከለቀቁ፣ የተወሰነ ጊዜ ገደብ ውል ለማለቅ ወደ 40% ብቻ ስለሆነ ታዲያ ለሌላ የማከራያ ክፍያ 40% ብቻ መክፈል አለብዎ።

  ወጪዎችን ስለመቆጣጠር

  ያለዎትን የኪራይ ኮንትራት ለማቋረጥ በተቻለ መጠን በጽሁፍ አድርጎ ብዙ ማስጠንቀቂያ መስጠት አለብዎ (የርስዎን ደብዳቤ ቅጂ ያስቀምጡ)። መቸ እንደሚለቁ ትክክለኛ ቀን መግለጹ ጥሩ ሲሆን ታዲያ ባለንብረቱ ወይም ተወካይ ድርጅት ሌላ አዲስ ተከራይ እንዲፈልግ ፍላጎትዎን ይገልጻሉ። አዲስ ተከራይን ቶሎ ብሎ ለማግኘት ባለንብረቱ የተቻለውን እርምጃ ሁሉ ለመውሰድ ይጠበቅበታል። አዲስ ተከራይ ለማግኘት በበለጠ መርዳት ከቻሉ (ማለት እንደ ቤቱን ለማሳየት ክፍት ማድረግ ወይም በራስዎ ቤቱን በማስታወቂያ ላይ ማውጣት) የሚከፍሉት አነስተኛ ሊሆን ይችላል።

  ቤቱን እስከሚለቁበት ቀን ብቻ የቤት ኪራይ መክፈል አለብዎ። አዲስ ተከራዮች መግባታቸውን ካወቁ በኋላ ላልተከፈለ የቤት ኪራይ ማካካሻ ገንዘብ ለባለንብረቱ መክፈል ይችላሉ።

  እርስዎ ማስጠንቀቂያ ከሰጡ በኋላ ቤቱን ለማከራየት በባለንብረቱ ወይም ተወካዩ በኩል እርምጃ ስለመወሰዱ ማረጋገጥና አዲስ ተከራይ የገባበትን ቀን ማጣራት አለብዎ። ባለንብረቱ ኪሳራቸውን የመቀነስ ግዴታ አለበት፤ ታዲያ አዲስ ተከራይ ለማግኘት አስቸጋሪ የሆነ ነገር ካደረጉ (እንደ የቤት ኪራይ መጨመር) ወይም አዲስ ተከራይ ለማግኘት ጥረት ካላደረጉ፤ ስለዚህ የማካካሻ ክፍያውን በሞላ ላለመክፈል መሟገት ይችላሉ።

  በአብዛኛው ጋዜጣ ላይ የሚከራይ በሚል ክፍል ወይም በተወካይ ድርጅቶች ላይ የወጣን ዝርዝር ቤቶችን ማየት። ኢንተርኔት ካለዎት በአከራይ ወኪል ድረገፅ ላይ ማየት ነው። ቤቱን ለማከራየት በማስታወቂያ ላይ ካልወጣ ወይም የቤት ኪራይ ዋጋ ተጨምሮ በማስታወቂያ ላይ ከወጣ፤ ይህንን እንደ ማስረጃ በመያዝ ስለዚህ ባለንብረቱ ስለሚኖረው ወጪ ለመቀነስ ጥረት አላደረገም ማለት ነው።

  በባለንብረቱ በኩል የተጠየቀ ወጪ ክፍያ አላግባብ ነው ብለው ካመኑበት ለመክፈል እንዳይስማሙ። ከዚያም ካለዎት የማስያዣ ገንዘብ ተቀንሶ እንዲሰጥ ይጠይቃል፤ እንዲሁም የማካካሻ ክፍያ እንዲሰጥ ለ Victorian Civil and Administrative Tribunal ልዩ ፍርድ ቤት ያመለክታል። በባለንብረት ስለቀረበው ጥያቄ ለርስዎ ማሳሰቢያ መስጠት አለበት፤ ስለዚህ በልዩ ፍርድ ቤት ችሎት ላይ የርስዎን ታሪክ ለማቅረብ እድል ያገኛሉ።

   ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

  ከዚህ ጋር የተዛመዱ ገጾች

  ለሌላ ማስተላለፍና ለሌላ ማከራየት

  ማስያዣ ገንዘብ

  ለማካካሻ ክፍያ ጥያቄ ስለመከራከር

  የተከራይ ውል ፍጻሜ

  የግዲታ መጣስ ማሳሰቢያ ለባለንብረትዎ ስለመስጠት

  መቸ ነው ቤቱን መልቀቅ የሚፈልጉ

  በበለጠ እርዳታ ይፈለጋልን?

  ተጨማሪ መረጃ ወይም እርዳታ ካስፈለግዎት እባክዎ እኛን ያነጋግሩ።


  Breaking a lease | Amharic | September 2011

  እኛን ያግኙን

  ለተከራዮች ምክር (advice for tenants)
  እኛን ያግኙን (contact us)

  የቪክቶርያ ተከረዮች | የተከራዮች የድጋፍ መስመር 03 9416 2577 | tenantsvic.org.au
  የቪክቶርያ ተከራዮች የቪክተርያ መንግስት ድጋፍ ዕውቅና ይሰጡታል፡፡

  Tenants Victoria acknowledges the support of the Victorian Government.