ለደንበኛ አገልግሎት መመሪያ

  ደህንነት

  ለደንበኞች፣ ለጎብኝዎችና ለሠራተኞች በሙሉ ደህንነቱ የተጠበቀና ከጭንቀት ነጻ የሆነ አካባቢ እናቀርባለን

  ለደንበኞች፣ ለጎብኝዎችና ለሠራተኞች በሙሉ ደህንነቱ የተጠበቀና ከጭንቀት ነጻ የሆነ አካባቢ እንዲፈጥር እርስዎ አስተዋጽኦ ያደረጋሉ

  ለሚከተሉት ምንም ትእግስት እንደሌለን:

  • ተቀባይነት የሌለው የአካል ግንኙነት
  • ሁከት ለሚፈጥር ማንኛውም ዓይነት ባህሪ
  • ትህትናን ማጣት፣ መዝለፍ መሳደብ፣ አንባጓረኛ ወይም የሚያስፈራራ ቋንቋ መናገር ወይም ባህሪ ማሳየት
  • በእኛ ህንጻ አካባቢ አልኮሆል ወይም አደገኛ እጽን መጠቀም ነው።

  ግላዊነት

  ከርስዎ የምንወስደውን መረጃ በሙሉ በሚስጢር እንጠብቃለን:

  • ግላዊ የሆነ መረጃ ከአውስትራሊያ ህግ ጋር ጠቃሚ በሆነ መልኩ እኛ መረጃ እንሰበስባለን፣ እናስቀምጣለን፣ እንጠቀማለ እንዲሁም የርስዎ ግላዊ የሆነን መረጃ ለሌላ አካል እናወጣለን።
  • እባክዎ የእኛን ግላዊነት ፖሊሲ የሚለውን ማየት

  ያለሠራተኛ አባል ለብቻዎ ወደ ሥራ አካባቢ መግባት አይገቡም

  ማክበር

  በማንኛውም ጊዜ እርስዎን ትህትና በተሞላበትና በክብር እናስተናግድዎታለን

  በማንኛውም ጊዜ የእኛን ሠራተኞች እና በአግልግሎቱ ውስጥ ያሉትን ሌሎች ሰዎች ትህትና በተሞላበትና በክብር ያስተናግዳሉ

  ግንኙነት

  እኛ አግባብ ባለው፣ ግልጽና ተግባራዊ በሆነ እንቀርባለን

  ለርስዎ ግልጽ፣ ትክክለኛ እና ወቅታዊ የሆነ መረጃ እንሰጣለን ወይም ከተቻለ እርስዎን መርዳታ ወደሚችል አገልግሎት እንልክወታለን።

  ማድረግ ያለብዎት:

  • በወቅቱ መረጃ ለእኛ ማቅረብ
  • ማንኛውም ለውቶች ሲከሰቱ ወዲያውኑ ለእኛ ዝርዝር መረጃ መስጠት
  • ለየት ያለ ፍላጎት ካለዎት ይንገሩን።

  የሚከተሉት ካለብዎት ለእኛ ለመናገር ነጻነት ይሰማዎት:

  • ስለ አገልግሎቱ የደረስዎ ቅሬታ/ክስ ካለ፤ ወይም በአግባብና በተገቢው መስተንግዶ አልተደረገልኝም ብለው ካሰቡ
  • ያለንን አገልግሎቶች እንዴት ማሻሻል እንደምንችል አስተያየት ካለ
  • ስለ አወንታዊ የሆነ ልምድ ተመኩሮ ምስጋና ጥሩ ምኞት

  በዚህ መመሪያ ለማይከተል ማንኛውም ደንበኛ ስለሚቀርቡለት አገልግሎቶች የተከራዮች ማህበር እምቢ ለማለት መብቱ የተጠበቀ ነው። ከህንጻው እንዲለቁ ሊጠየቁ እንድሚችሉና በሌላ ጊዜ እንዲመለሱ ይደረጋል። ከህንጻው እንዲሄዱ ሲጠየቅ መሄድዎን ለማረጋገጥ እርምጃዎችን ልንወስድ እንችላለን።


  Client service charter | Amharic

  Tenants Victoria acknowledges the support of the Victorian Government.