በቤት ነዋሪዎች ውስጥ ‘ጓደኛ’ ማስቀመጥ - Tenants Victoria

በቤት ነዋሪዎች ውስጥ ‘ጓደኛ’ ማስቀመጥ

በደባል መኖሪያ ቤት ከሌሎች ሰዎች ጋር መኖር የቤት ኪራይና ሌሎች የፍጆታ ወጪዎችን አብሮ ለመክፈል ለብዙዎች ጥሩ ዘዴ እንደሆነና ለብቻ ከመኖር በበለጠ አስደሳች ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ በቤት ውስጥ ነዋሪ አባላት መካከል አለመግባባት ሲፈጠር በተለይ አብሮ መኖርን የሚቀጥሉ ከሆነ መፍትሄ ለማግኘት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።

የሚኖሩት በምን ዓይነት የመዳበያ መኖሪያ ቤት ነው?

እርስዎ መምረጥ ወይም መግባት የሚችሉበት የተለያየ ዓይነት ሰዎች በአንድ ቤት አብሮ የሚኖርበት ቤቶች አሉ። ሁሉም የመዳበያ ቤቶች አንድ ዓይነት ስላልሆኑ፤ ስለዚህ የርስዎ ምርጫ በሚኖርዎ ህጋዊ መብቶችና ሃላፊነቶች ይወሰናል።

ከባለንብረቱ ወይም ከንብረት ተወካዩ ጋር የተከራይና አከራይ ውል ስምምነት (ብዙጊዜ ‘ውል’ ይባላል)፤ ቢያንስ ከአንድ ሌላ ተከራይ ጋር ሆነው ፈርመው ከሆነ ‘በአብሮ ተከራይ/co-tenancy’ ውል ገብተዋል ማለት ነው። እንደ አብሮ ተከራይ መሆንዎ መጠን ለቤት ኪራይ መክፈል፣ ህጋዊ የሆኑ ግዴታዎችን ከሌሎች ተከራዮች ጋር በእኩል ሃላፊነት መወጣት አለብዎ።፡ አብሮ ተከራይዎች ‘በተከራይና አከራይ ውል መሰረት በጋራ ከፍተኛ የንብረት ሃላፊነት ይኖራቸዋል። ይህ ማለት ላልተከፈለ ጠቅላላ የቤት ኪራይ ወይም ‘ግዴታን በአግባቡ ባለመወጣት ምክንያት የካሳ ክፍያን (እንደ በንብረት ላይ ለደረሰ ጉዳት) ባለንብረቱ ለሁሉም አብሮ ተከራዮች ወይንም ለእያንዳንዱ ተከራይ ጥያቄ ማቅረብ ይችላል።

ምንም እንኳን ስምዎ በውሉ ላይ አይጠቀስ እንጂ በሌላ ተከራይ ለመዳበል ‘ከተመደቡ’ (ከባለንብረቱ ጋር በቅድሚያ ስምምነት ከተደረገ በኋላ) እና በቤት ውስጥ ስለመኖርዎ ባለንብረቱ ወይም የንብረት አከራይ ድርጅት ካወቀ በአብሮ ተከራይነት ሊመደቡ ይችላሉ። ብዙጊዜ በሌላ ተከራይ የተከፈለው የማስያዣ ገንዘብ ወደ እርስዎ ስም ይተላለፋል።

እንዲሁም ‘በምክትል የተከራይነት’ ስምምነት’ መሰረት በደባልነት ለመኖር መግባት ይችሉ ይሆናል። የርስዎ ቤት ኪራይ በሌላ ተከራይ (ዋና ተከራይ) ከተሰበሰበ ‘ምክትል ተከራይ’ በሚል ስም ሊታወቁ ይችላሉ። በምክትል ተከራይና በዋና ተከራይ መካከል በተከራዩት ንብረት ላይ የሚፈጠር ክርክር በተከራይና አከራይ ህግ ውስጥ ይካተታል። ይህም በህጉ ለመመራት ሲባል ምክትል ተከራይ የሚባለው ተፈጥሮ ከነበር ነው። አብሮ ተከራይ ብዙጊዜ ከባለንብረት ወይም ከንብረት ተወካይ ጋር በቀጥታ ድርድር አይደረግም። እንደ አብሮ ተከራይ ሆኖ ወደ ቤቱ ከመግባትዎ በፊት ባለንብረቱ ወይም ንብረት ተወካዩ እርስዎ እንዲገቡ ፍቃድ ለዋናው ተከራይ በጽሁፍ ስለመሰጠቱ ማረጋገጥ አለብዎ።

ከባለንብረቱ ወይም ከዋናው ተከራይ ጋር ተዳብለው ( ‘ቤት ውስጥ / homestay’) የሚኖሩ ከሆነ ታዲያ ‘የፈቃድ/licence’ ስምምነት በመባል ሊታወቅ ይችላል። በዚህ ሁኔታ ላይ እንደ ተከራይ

መሆን አይቆጠሩም፤ ስለዚህ በህጉ መሰረት እንደ ተከራዮች እኩል እንክብካቤ አይኖርዎም። በዚህ አካባቢ ያለው ህግ የተወሳሰበ በመሆኑ የተወሰነ ምክር መጠየቅ ያስፈልግዎታል።

ለአራት (4) ወይም ከዚያ በላይ ሰዎች አንድ ወይም ሁለት ክፍል ባለው መዳበያ መኖሪያ ቤት ኪራይ የሚኖሩ ከሆነ፤ ‘በራስ ክፍል መኖሪያ/rooming house resident’ በመባል ሊታወቅ ይችላል። በክፍል ውስጥ ነዋሪዎች እና በባለንብረቱ ወይም አስተዳዳሪው መካከል አለመግባባት ሲፈጠር ነዋሪዎች ህጋዊ የሆነ መከላከያ ይኖራቸዋል።

የሚከሰቱ ችግሮችን እንዴት መፍታት ይችላሉ?

በመዳበያ መኖሪያ ቤት የሚኖሩ ከሆነና ከባለንብረቱ ወይም ተወካዩ ጋር ያለመግባባት ከተፈጠረ፣ ወይም ስለሚኖሩበት መዳበያ ቤት ዓይነት እርግጠኛ ካልሆኑ ነጻና ምስጢራዊ በሆነ ምክር ከቪክቶሪያ የተከራይ ማሕበር (Tenants Union of Victoria/Tenants Victoria) ማግኘት ይችላሉ። እንዲሁም የተከራይ ማሕበርን ማየቱ ጥሩ ዘዴ ይሆናል ወይም ስለ ቤት ኪራይ ውል ቅድመ ሁኔታዎች እርግጠኛ ካልሆኑ የተከራይና አከራይ ኮንትራት ውል ከመፈረምዎ በፊት ህጋዊ የሆነ ምክር ያስፈልግዎታል።

የርስዎ ክርክር ከአብሮ ተከራይ ጋር ከሆነ፤ የአብሮ ተከራይ ስምምነት ህግ በተከራይና አከራይ ውል ስምምነት የማይካተት በመሆኑ ለዚህ መፍትሄ ማግኘት አስቸጋሪ ሲሆን ይችላል። የርስዎ ክርክር ከሌላ ተከራይ ጋር ከሆነ ከማሕበረሰብ ህጋዊ ማእከል/ Community Legal Centre ምክር ማግኘት ይችላሉ ወይም ከቪክቶሪያ የክርክር መፍትሄ ማስገኛ ማእከል/ Dispute Settlement Centre of Victoria እርዳታ ማግኘት ይችላሉ። ብዙ ጊዜ የተፈጠርውን ችግር ለመቅርፍ በቶሎ ምክር ማግኝት ይጠቅማል፡፡

በደባል መኖሪያ ቤት ሲኖሩ ግምት ውስጥ መግባት ያለበት

በደባል መኖሪያ ቤት ሲኖሩ የጋራ ችግሮችን ለማስወገድ የሚከተሉትን ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል:

በደባል ነዋሪ ባለበት ቤት ውስጥ ስለመግባት

 • ወደ ቤቱ እንዲገቡ ባለንብረቱ ተስማምቷልን?
  ይህ በጽሁፍ ነው? በህጉ መሰረት፤ በንብረቱ ሌላ ሰው በሚገባበት ጊዜ ለባለንብረት ወይም ንብረት ተወካይ ማወቅ ሲኖርበት፤ እንዲሁም የእነሱን ፍቃደኝነት በጽሁፍ ማግኘት አለብዎ።
 • ወቅታዊ የሆነ የተከራይና አከራይ ኮንትራት ውል አለ?
  ውል ካለ፡ ከቤቱ ነዋሪዎች ጋር እኩል መብት እንዳለዎ ለማረጋገጥ ስምዎን በኮንትራት ውሉ ላይ ማስገባት ይፈልጉ ይሆናል። ያስተውሉ፡ በስምምነት ውሉ መሰረት በጋራ ለብዙ ነገሮች ሃላፊነት ትወስዳላችሁ ማለት ነው።
 • የማስያዣ ገንዘብ ከፍለዋልን? ለማን?
  ከሌላ ሰዎች ጋር ለመኖር ወደ ቤ ሲገቡ ብዙጊዜ ለማስያዣ ገንዘብ ድርሻዎን እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ። ታዲያ የማስያዣ ገንዘብ ሲከፍሉ በማስያዣ ማስተላለፊያ ቅጽ (Bond Transfer form) ላይ ስለመፈረምዎ በማረጋገጥ ለከፈሉት የገንዘብ መጠን የሚገልጽ ደረሰኝ ማግኘት አለብዎ።
 • ወደ ቤቱ ከገቡ በኋላ መክፈል ያለብዎ ምን ዓይነት ሌላ የፍጆታ ክፍያዎች እንዳሉ አጣርተዋልን?
  ለተለፎን፣ ጋዝ፣ ኤሌትሪክና ለሌላ መገልገያ ፍጆታ ክፍያዎች በቤቱ ውስጥ በሚኖሩ ሰዎች መካከል ይከፋፈላል። በነዚህ የፍጆታ ክፍያ መጠየቂያ ላይ የነማን ስም እንዳለ ማጣራትና ለኑሮ የሚያስፈልግዎን በርስዎ ባጀት ውስጥ ማካተት።
 • በአሁን ጊዜ በመኖሪያ ቤት ውስጥ ደንቦች አሉን?
  በአንዳንድ ደባል መኖሪያ ቤት ያሉ ተከራዮች በተሻለ አባሉን ለማስተዳደር የራሳቸውን ደንቦች ያወጣሉ። ለቤት ጽዳት፣ ምግብ ማብሰልና ምግብ ለመግዛት ተራ በቤት ውስጥ ደንቦች ላይ ሊካተት ይችላል። እንዲሁም የፍጆታ ክፍያ እንዴት መክፈልና አንድ ሰው ቤቱን መልቀቅ ከፈለገ እንዴት ማሳሰቢያ እንደሚሰጥ በደንቦቹ ውስጥ ይካተታሉ። ወደ ቤቱ ከመግባትዎ በፊት የቤት ውስጥ ደንቦች ካሉ ታዲያ እነዚህን ስለመረዳትዎና መስማማትዎ ማረጋገጥ ይኖርብዎታል።

ከነዋሪዎች ጋር አብሮ ለመዳበል ቅንጅት

በአንዳንድ ሁኔታ ላይ ከሌሎች ሰዎች ጋር የደባል መኖሪያ ቤትን ይመርጡ ይሆናል። ከተቻለ የቤት ኪራይና የፍጆታ ክፍያን አብሮ መካፈል ከሚችል የሚያውቁት ሰው ጋር አብሮ መግባት ጥሩ ነው። በቤት ውስጥ ነዋሪዎች ሁሉም እኩል መብቶችና ሃልፊነቶች እንዲኖራቸው ለማረጋገጥ ስማቸውን በኮንትራት ውል ውስጥ ማስገባት አለብዎ።

ከጊዜ በኋላ የሚከሰትን አለመግባባት ለማስወገድ እርስዎና በቤት ውስጥ ነዋሪዎች ስለሚኖር ተግባራት ስምምነት ላይ መድረስ ጥሩ ዘዴ ነው። ያለመግባባትን ለማስወገድ እንዲረዳ ስምምነቱን በጽሁፍ አድርጎ እያንዳንዱ ነዋሪ እንዲፈርምበት ማድረግ ነው። የስምምነት ውሉ

የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል:

 • እያንዳንዱ ምን ያህል የቤት ኪራይ መክፈል እንዳለበት?
  ብዙጊዜ የቤት ኪራይ እኩል ይከፈላል ወይም አንድ ሰው ትልቅ የመኝታ ክፍል ካለው ከፍተኛ የቤት ኪራይ ሊከፍል ይችላል።
 • የፍጆታ ክፍያው እንዴት እንደሚከፋፈልና እንደሚከፈል?
  በፍጆታ መክፈያዎች ላይ የማን ስሞች እንዳለ? የስልክ ክፍያን ለመከፋፈል ዘዴ ለማውጣት ያስፈልግዎት ይሆናል (ለምሳሌ፡ እያንዳንዱ ሰው ባደረገው የስልክ ጥሪ መነሻ በማድረግ)።
 • እንዴት ገንዘቡ ይሰበሰባል?
 • ለቤት ነዋሪዎች የሚያስፈልግ ወጭ መዋጮ አለ ለምሳሌ፡ ለሸቀጣሸቀጥ መግዣ?
 • ለቤት ነዋሪዎች መገልገያ የሚሆን ቤት እቃዎች ማን ያቀርባል?
  እያንዳንዱ ነዋሪ ማቅረብ ያለበትን እቃዎች መግለጹ የተሻለ መንገድ ይሆናል። አንዳንዴ ሰዎች የኤሌትሪክ መገልገያዎችን ስለሚከራዩና ወጪውን ስለሚከፋፈሉ ነው። ለርስዎ የሚያስፈልግ ሌላ የቤት መገልገያ እቃዎች ካሉ፤ ስለዚህ እያንዳንዱ ነዋሪ በግሉ የሚፈልገውን ለብቻው መግዛት ይችላሉ።

ከቤት ነዋሪዎች ጋር ተዳብሎ ስለመኖር

አብሮ ለመኖር ወደ ቤት ከመግባትዎ በፊት ለርስዎ ፍላጎት ተስማሚና ለወደፊት የሚከሰት አለመስማምት ያስወዳል ካሉ በቅድሚያ በቅንጅት ስለመኖር መወያየት ጠቃሚ ነው።

 • ከቤት ካሉት ነዋሪዎች በጋራ ወይንስ ለብቻዎ ሆኖ ለመኖር ነው?
  አብረው ገብያ መሄድና አብሮ ምግብ ማብሰል ይፈልጋሉ ወይንስ ለብቻዎ? የተለያዩ ነዋሪዎች በጣም የተለያየ ግምት ሊኖራቸው ይችላል።
 • ተቀባይነት ያለው የድምጽ ደረጃ ማለት ምንድ ነው?
  እርስዎና በቤቱ ነዋሪዎች የተለያየ የአኗኗር ዘዴዎች ካሉ ይህ ችግር ሊፈጥር ይችላል። ስለ ድምጽ ድረጃ ምን ያህል እንደሆነ ወደ ቤቱ ከመግባትዎ በፊት ግልጽ የሆነ መመሪያ ማግኘት ጠቃሚ ነው። ከፍተኛ ድምጽ ተቀባይነት ከሌለው በማታና በጥዋት የጊዜ ገደብ ለማድረግ መስማማቱን ይመርጡ ይሆናል።
 • እርስዎ ወይም የቤት ነዋሪ ጓደኞች ከመጡ ምን ይደረጋል?
  እንግዶች (ለምሳሌ፡ ጓደኞች፣ ቤተሰብ ወይም የትዳር ጓደኛ) ለኑሮ የሚያስፈልግ ወጪዎች ማለት የቤት ኪራይና የፍጆታ ክፍያ ከማዋጣታቸው በፊት ምን ያህል እንደሚቆዩ መስማማቱ ጥሩ ነው።
 • የቤት ኪራይና የፍጆታ ክፍያ ለመክፈል የማን ሀላፊነት ነው?
  የቤት ኪራይና የፍጆታ ክፍያ እንዴት ይከፋፈላል? በቅርቡ ስላለው የክፍያ አማራጭ ከተለፎንና ከመገልገያ ኩባንያዎች ጋር ማረጋገጥ አለብዎ ለምሳሌ፡ በየወሩ መክፈል ከቻሉ። ለሁሉም ክፍያዎች ደረሰኝ ስለማግኘትዎ ያረጋግጡ።

ከደባል መኖሪያ ቤት ስለመልቀቅ

አንድ ሰው ነዋሪዎችን ትቶ መሄድ ከፈለገ ምን ይደረጋል? የተከራይና አከራይ ስምምነት ውል ጊዜ ከማለቁ በፊት ከቤት ነዋሪዎች ውስጥ አንደኛው አባል ለመውጣት ሲፈልግ ችግር መፈጠር የተለመደ ነው። ግልጽ የሆነ ስምምነት በማካሄድ ችግሩን ማስወገድ ይቻላል፤ ይህም አንድ ሰው ለመልቀቅ ከፈለገ ለምን ያህል ጊዜ ማሳሰቢያ መስጠት እንዳለበት፤ ለአዲስ ተከራይ ማን እንደሚያነጋግርና ለባለንብረቱ ወይም ለንብረት ተወካዩ ለመናገር ማን ሃላፊነትን እንደሚወሰድ ይሆናል።

ስምዎ በኮንትራት ውሉ ውስጥ ካለ ውሉ እስካለቀበት ጊዜ ወይም አዲስ ተከራይ እስኪገባ ድረስ የቤት ኪራይ ለመክፈል የርስዎ ሃላፊነት ይሆናል።

በበለጠ መረጃ ለማግኘት የእኛን Shared households (በደባል ነዋሪዎች) እና Assignment & sub-letting (ለሌላ ማስተላለፍና ለሌላ ማከራየት) የሚለውን እውነታ ጽሁፍ ወረቀት ማየት።

ከቤት ነዋሪዎች ጋር አብሮ ለመሥራት አንዳንድ ምክሮች

 • ፊት ለፊት መነጋገር፣ አከራካሪ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት በቂ ጊዜ መውሰድ
 • ጉዳዩ የቤቱን ነዋሪዎች በሞላ የሚያካትት ከሆነ በቤት ነዋሪዎች ስብሰባ ለማካሄድ አመቺ ጊዜ ማቀናጀት ሊፈልጉ ይችላሉ
 • ችግሩ ምን እንደሆነ በግልጽ ማስቀመጥና ሳይበሳጩ ረጋ ለማለት መሞከር
 • ለችግሩ በግለሰብ ላይ ከማማረር ፋንታ ችግር ስለሆነው ጉዳይ ወይም ሁኔታ ላይ መወያየት
 • ነዋሪዎቹ የሚሉትን በጥንቃቄ ማዳመጥና እነሱን ላለማደናቀፍ መሞከር
 • ማንኛውም የቤት ውስጥ ደንቦች ተጥሰዋል ብለው ካሰቡ ማየት
 • ለችግሩ መፍትሄ በሚሆን ጉዳይ ላይ መወያየት
 • ችግሩን ለመፍታት እያንዳንዱ በሚወስደው እርምጃዎች ላይ መስማማት

ችግሩ መፍትሄ ማግኘት ካልቻለ በክርክር መፍትሄ ማእከል (Dispute Settlement Centre) በኩል አንዳንድ አስተያየቶችን ሊቀርብልዎ ይችላል፤ ወይም በእርቅ ድርድር ሌላው ነዋሪ ለመምጣት ከተስማማ ስብሰባ ይቀናጃል። ይህም ለችግሩ መፍትሄ እንድታገኙ ተጽእኖ በሌለበትና በራሱ በሚመራ አስታራቂ በኩል የቤቱ ነዋሪ አባላት የተገኙበት ስብሰባ ይካሄዳል።

የእርቅ ድርድሩ ተስማሚ ካልሆነ ወይም ጥሩ ውጤት ካላመጣ ምክር ለማግኘት የማህበረሰብ ህግ ማእከልን (Community Legal Centre) ማነጋገር ይችላሉ።

ለእርዳታ የት እንደሚኬድ

በቪክቶሪያ የተከራይ ማሕበር (Tenants Union of Victoria/Tenants Victoria) ከርስዎ ባለንብረት ወይም የንብረት ተወካይ ጋር ስለቤት ከራይ ክርክር በነጻ ህጋዊ የሆነ ምክር ለማግኘት።
1800 068 860
ድረገጽ፡ www.tuv.org.au

በፈደሬሽን የማህበረሰብ ህግ ማእከላት (Federation of Community Legal Centres) በአብሮ ተከራይ ባለ ክርክር በአካባቢዎ በነጻ ህጋዊ የሆነ ምክር አቅራቢ የህግ ማእከል ለማግኘት ለፈደሬሽን መደወል።
9652 1500
ድረገጽ፡ www.communitylaw.org.au

በቪክቶሪያ ለክርክር መፍትሄ ፈላጊ ማእከል (Dispute Settlement Centre of Victoria)
ከርስዎ በቤት አብሮ ነዋሪ ጋር ያለን ክርክር ለመፍታት እንዲረዳዎ የነጻ እርቅ አገልግሎት ለማግኘት፡
1300372888 (በነጻ 1300372888 ከመልበርን ውጭ ሆኖ ለመደውል)
ድረገጽ፡ www.disputes.vic.gov.au

በቪክቶሪያ እኩል እድልና ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (Victorian Equal Opportunity & Human Rights Commission) በባለንብረቱ ወይም በንብረት ተወካዩ አድልዎ ደርሶብኛል ብለው ካመኑ የነጻ ምክር ለማግኘት፡
% 1300 292 153
ድረገጽ፡ www.equalopportunitycommission.vic.gov.au

የተከራይ ነዋሪዎች ማስያዣ ባለስልጣን (Residential Tenancies Bond Authority) ስለርስዎ የማስያዣ ገንዘብ ለመጠየቅ፡
1300 137 164
ድረገጽ፡ www.rtba.vic.gov.au

ለተማሪ አገልግሎት (Students Services) እርስዎ በሚማሩበት አካባቢ ምክርና ድጋፍ ሊሰጥዎ የሚችል ለተማሪ መኖሪያ ቤት አገልግሎት፣ ለዓለም አቀፍ ተማሪ አገልግሎት ወይም የህግ አገልግሎት ስለመኖሩ ያጣሩ።

በስልክ የአስተርጓሚ አገልግሎት ከዚህ በላይ ላሉ ድርጅቶች ለመደወል የአስትርጓሚ እርዳታ ካስፈለግዎ፡
131 450 (በቀን ለ24 ሰዓታት, በሳምንት ለ7 ቀናት)

 ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

በበለጠ እርዳታ ይፈለጋልን?

ተጨማሪ መረጃ ወይም እርዳታ ካስፈለግዎት እባክዎ እኛን ያነጋግሩ።


Keeping the mates in house mates | Amharic | October 2011

እኛን ያግኙን

ለተከራዮች ምክር (advice for tenants)
እኛን ያግኙን (contact us)

የቪክቶርያ ተከረዮች | የተከራዮች የድጋፍ መስመር 03 9416 2577 | tenantsvic.org.au
የቪክቶርያ ተከራዮች የቪክተርያ መንግስት ድጋፍ ዕውቅና ይሰጡታል፡፡

Tenants Victoria acknowledges the support of the Victorian Government.